Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 290 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 137 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 347 የላብራቶሪ ምርመራ 290 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
እንዲሁም 1 ሺህ 137 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
ይህም ወረርሽኙ ከገባ ጀምሮ እስካሁን 104 ሺህ 818 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን መረጃው ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት የ3ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 864 ደርሷል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 752 ሺህ 252 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 120 ሺህ 638 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 954ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 274 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም መረጃው ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.