Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 355 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 989 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 725 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 355 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ እንዳስታወቁት 332 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ከዚህ ባለፈም 989 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 103 ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት የ4 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 512 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 514 ሺህ 896 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተካሄደ ሲሆን 98 ሺህ 746 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.