Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 388 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 91 የላቦራቶሪ ምርመራ 388 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 106 ሺህ 591 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈም የ10 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 661 መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 179 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ሺህ 18 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 604 ሺህ 697 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 106 ሺህ 591 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 38 ሺህ 910 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 334 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.