Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 488 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 960 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 866 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 488 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 95 ሺህ 789 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ የ7 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 464 መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 960 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 51 ሺህ 713 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 474 ሺህ 983 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 95 ሺህ 789 ደርሷል።
በሌላ በኩል ደግሞ 327 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.