Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 524 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 79 ሰዎች አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ 524 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 79 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 381 የላቦራቶሪ ምርመራ 524 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 128 ሺህ 316 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 79 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 113 ሺህ 374 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 994 ደርሷል።

ቫይረሱ ካለባቸው 12 ሺህ 946 ሰዎች መካከል 202 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ ሲሆኑ እስካዛሬ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 850 ሺህ 100 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.