Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 533 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 670 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ 533 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 670 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ 12 ሺህ 241 ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 236 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 709 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 533 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 122ሺህ 413 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 670 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 ሺህ 269 መድረሱንም ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የአራት ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 901 ደርሷል።

በሃገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 776ሺህ 322 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.