Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 544 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 108 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ6 ሺህ 284 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 544 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው እለታዊ መረጃ 1 ሺህ 108 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውንም አስታውቋል።
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 12 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 96 ሺህ 307 ሲደርሱ 1 ሺህ 843 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
አሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 16 ሺህ 331 ሲሆኑ 261 ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 731 ሺህ 977 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.