Fana: At a Speed of Life!

ቱርካውያን አትሌቶች ለቶኪያ ኦሊምፒክ በኢትዮጵያ ልምምድ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርካውያን አትሌቶች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ሚኒማ ለሟሟላት በኢትዮጵያ በከፍታማነታቸው ከሚጠቀሱት ቦታዎች መካከል አንዱ በሆነው ሱሉልታ ልምምድ እያደረጉ ነው።

አትሌቶቹ ለቶኪዮ ማራቶን እና ለ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ የሚያስፈልጋቸው ሚኒማ ለሟሟላት ነው ልምምዳቸውን በኢትዮጵያ እየሰሩ የሚገኙት።

የ2020 ኦሊምፒክ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መራዘሙ የሚታወስ ሲሆን በፈረንጆቹ ሀምሌ ወር 2021 ጀምሮ በቶኪዮ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የአትሌቶቹ የቡድን መሪዎች ቢላል አርስላን እና ኤልቫን አቢይለገስ ቱርክ በማራቶን እና በ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ምርጥ ሰዓት ያላቸውን 12 አትሌቶች መርጣለች ብለዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አስሩ የማራቶን አትሌቶች ሲሆኑ ሁለት አትሌቶች ደግሞ 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ለመወዳደር ልምምድ እየሰሩ እንደሚገኙ ያኒ ሳፋክ አናዶሉን ጠቅሶ ዘግቧል።

የአሁኑ ልምምዳቸው  በየካቲት ወር በቱርክ ትራብዞን ለሚካሄደው ውድድር ሲሆን ይህ ውድድር አትሌቶቹ ለቶኪዮ አሊምፒክ ሚኒማ ለሟሟላት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

በዚህ ውድድር ሚኒማቸውን የሚያሟሉ አትሌቶችን በመያዝም ከአምስት ወራት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በድጋሚ እንደሚመለሱ ተጠቁሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.