Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ልትጥል ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ የኮቪድ19 ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ልትጥል ነው።

የሃገሪቱ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትና የሞት መጠኑን ለመቀነስ ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችን እንደሚጥል አስታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎም አሁን ላይ የሀገሪቱ ጎዳናዎች  እና የገበያ ማዕከሎች በሰዎች መጨናነቃቸው ነው የተነገረው።

አንዳንዶቹ ከኢስታንቡል ለመውጣት ወደ ዋናው የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ሲጎርፉ፥ ገሚሶቹ ሊኖር ይችላል የተባለውን የመጠጥ ክልከላ በማሰብ አልኮል መጠጦችን ሲገዙ ተስተውለዋል፡፡

ቱርክ ባለፈው ዓመት  ወረርሽኙን ቀድሞ በመከላከል  ረገድ የተሳካላት ሀገር ስትሆን በዓለም የጤና ድርጅትም ለዚህ ስኬቷ ውዳሴ አግኝታለች፡፡

በቱርክ በሚያዝያ ወር በቀን ከ60 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ ከ300 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ያልፋል ተብሏል ።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.