Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በስዊድን እና ፊንላንድ የኔቶ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ እንዳይሰጥ አገደች

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ለመሆን ዛሬ በይፋ ባቀረቡት የጽሑፍ ማመልከቻ ላይ ቱርክ ባለመስማማቷ ሂደቱ እንዲታገድ ማድረጓ ተገለጸ።
ስዊድን እና ፊንላንድ የወታደራዊ ቃል ኪዳኑ ድርጅቱ አባል ለመሆን ያቀረቡትን ማመልከቻ ለመጀመሪያ ጊዜ በማየት ላይ የነበሩት የኔቶ አባል ሀገራት አምባሳደሮች በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት ድምጽ እንዳይሰጡ በአንካራ በኩል ተቀውሞ ገጥሟቸዋል ሲል ፋይናንሽያል ታይስ ዘግቧል።
የሀገራቱ የአባልነት ጥያቄ ቢራዘም እንኳ በአንድ ወይም በሁለት ሳምንት ውስጥ ሊያልቅ እንደሚችል የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጀንስ ስቶልተንበርግ አመላከትውት የነበረው ተስፋ እንደጨለመም ነው ዘገባው የገለጸው።
የጉዳዩ መራዘም በአሜሪካ፣ ቱርክ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ መካከል ረዘም ላሉ ቀናት ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ማድረግ እንደሚጠይቅ ዘገባው አመልክቷል።
በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የቱርክ ባለስልጣን በሰጡት አስተያየት፥ አገራቸው የምትሻውና የምታስቀድመው ሰላሟንና ደህንነቷን መሆኑን ገልጸው፥ “ እኛ አገራቱ ከነጭራሹ የኔቶ አባል አይሆኑም የሚል አቋም የለንም፤ ነገር ግን አንድ ገጽ ላይ ሆነን ያለብንን ስጋት ልንጋራ ይገባል” ብለዋል።
በቅድሚያ ስምምነት ላይ ልንደርስ ይገባል ያለችው ቱርክ፥ ስምምነት ላይ እንደደረስን የሀገራቱ የአባልነት ጥያቄ ላይ መወያየት እንችላለን የሚል አቋሟን ገልጻለች።
ቱርክ ከዚህ ቀደም በህግ የምትፍልጋቸውንና ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ክስ የመሰረተችባቸውን 30 ግለሰቦች ስዊድን እና ፊንላንድ አሳልፈው ሊሰጡኝ ይገባል የሚል አቋም ስታራምድ ቆይታለች።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.