Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በወጣቶች ላይ ሰዓት እላፊ ገደብ ጣለች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በወጣቶች ላይ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሏን አስታወቀች።

ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እድሜታቸው ከ20 አመት በታች በሆኑ ወጣቶች ላይ ሰዓት እላፊ መጣሉን አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንካራና ኢስታንቡልን ጨምሮ ወደ 31 ከተሞች አስፈላጊ ከሆኑ ጉዞዎች ውጭ ሰውም ሆነ ተሽከርካሪ መግባት እና መውጣት እንደማይችልም ይፋ አድርገዋል።

እገዳው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎች በሚኖር እንቅስቃሴ ወቅት የፊት ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው ተብሏል።

እገዳው እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ ሊራዘም እንደሚችልም ኤርዶኻን ገልጸዋል።

በቱርክ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጤና እክል ያለባቸውና እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉ ይታወሳል።

የአሁኑ እርምጃም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ያለመ ነው ተብሏል።

እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ በቱርክ 425 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.