Fana: At a Speed of Life!

ታሊየም የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ መረጃ መዝባሪዎች ቡድን ሚስጢራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር ነበር – ማይክሮ ሶፍት

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ታሊየም የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ መረጃ መዝባሪዎች ቡድን ሚስጢራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር እንደተቆጣጠረው ማይክሮ ሶፍት አስታወቀ፡፡

መቀመጫው ሰሜን ኮሪያ እንደሆነ የታመነው ይህ መረጃ መዝባሪ ቡድን የመንግስት ሰራተኞችን ፣ የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችን ፣ የኒውክሌር ሙያተኞችን እና የጥናት ተቋማንን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የመረጃ መዝባሪ ቡድኑ በዋነኝነት ኢላማ ያደረገው በአሜሪካ የሚገኙ ተቋማትን ሲሆን በጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ተቋማንንም ኢላማ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

ታሊየም በመጀመሪያ እይታ ትክክለኛ ሆነው የሚታዩ የኢሜል አድራሻዎችን  በመጠቀም   መረጃ ሲመዘብር ነበር ተብሏል፡፡

ማይክሮሶፍትም በአሁን ወቅት መረጃ መዝባሪ ቡድኑ የሚጠቀምባቸውን 50 የድር ጎራዎች መቆጣጠሩን የገለፀ ሲሆን በምሥራቃዊ ቨርጂኒያ አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት በጠለፋ ቡድን ላይ  ክስ መመስረቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.