Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከደለል ለመጠበቅ ሁሉም አረንጓዴ አሻራውን ሊያሳርፍ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁን የኢትዮያጵያ ህዳሴ ግድብ ከደለል ለመጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ለመቀነስ ሁሉም አረንጓዴ አሻራውን ሊያሳርፍ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን የውጫሌ ውል በተፈረመበት ታሪካዊው ቦታ ይሰማ ንገስ ላይ አሳርፈዋል፡፡
የተቋሙ ሰራተኛች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ሁሉም ዜጋ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተጽዕኖ መቀነስ አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለምን ጣሰው በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያውያን ችግኝ በመትከል እንደ ታለቁ ህዳሴ አይነት ግድቦችን ከደለል ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።
ችግኝ ከመትከል ባለፈ እንክብካቤ ማድረግም ትኩረት ሊሠጠው የሚገባ ተግባር መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል የተቋሙ ሰራተኛች ችግኝ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ተፈናቅለው ለመጡና በሀይቅ ከተማ ጃሪ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች 50 ሺህ ብር የሚያወጣ የአልባሳትና የምግብ ዱቄት ድጋፍ አድርገዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.