Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢድ ሰላትን በኢትዮጵያ ለማክበር የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪ ጋር በተያያዘ ከተዘጋጁ መርሀ ግብሮች መካከል አንዱ በሆነው ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ ላይ ለመታደም የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች አዲስ አበባ ገቡ፡፡

ተወካዮቹ የደቡብ ሱዳንና የጂቡቲ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አመራሮች ሲሆኑ፥ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢድ እስከ ኢድ ጥሪን እንዲያስተባብር የተቋቋመው ኮሚቴ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለታላቁ የኢድ ስግደት በኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራትና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መጋበዛቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.