Fana: At a Speed of Life!

ታዋቂዎቹ ተዋናዮች ጆአና ሉምሌይና ዞይ ዋናሜከር በኢትዮጵያ ልዩ የሆነውን ዛፍ ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂዎቹ ብሪታኒያዊ ተዋናዮች ጆአና ሉምሌይ፣ ዞይ ዋናሜከር እና የዱር እንስሳት ባለሙያ እና መብት ተሟጋች በኢትዮጵያ የዕጣን እና ሙጫ ዛፍን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ሊያደርጉ ነው።

ትሪ ኤድ የተሰኘ የተራድኦ ድርጅት በመተማ ወረዳ የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የተራቆተውን 10 ሺህ ሄክታር የአካባቢውን ደን ለማልማት እየተንቀሳቀሰ ነው።

በዚህ እንቅስቃሴም ሶስቱ ታዋቂ ሰዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ድጋፉ በመተማ የሚገኘውን የዕጣን ዛፍ እና ሙጫ ዛፍ (ቦስዌሊያ) ጥበቃ ለማድረግ  መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ይህ ዛፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለቆዳ ጤና ወሳኝ የሆነ ዘይት ማምረት የሚያስችል ሲሆን አሁን ላይ ጥበቃ ካልተደረገለት በ20 ዓመታት ውስጥ ሊጠፋና አካባቢውም ሙሉ በሙሉ በረሃማ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።

ይህ ደግሞ ከአካባቢው አልፎ በሰሃል ቀጠና ለሚገኙ ነዋሪዎች ተፅዕኖው የጎላ መሆኑን ዘገባው ያመላክታል፡፡

በአረቢያ ፔኒንሱላ እና በአፍሪካ ቀንድ ብቻ የሚገኘው ዛፉ አሁን ላይ በአፈር መሸርሸር ፣ በሙቀት መጨመር እና ከሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ አምራቾቹና ምርቱ ለአደጋ ተጋልጠዋል ተብሏል።

ትሪ ኤድም 3 ሺህ ቤተሰቦችን በማሳተፍ ከዚህ የዛፍ አይነት የሚያገኙትን ገቢ በ25 በመቶ ለመጨመር እና 9 ሺህ 563 ሄክታር መሬትን መልሶ በደን ለመሸፈን እንደሚሰራ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.