Fana: At a Speed of Life!

ታዳጊ ሀገራት በዓለምአቀፍ መድረክ ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል – ቻይና

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራቸው እንደሚገባ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ገለጹ፡፡

ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፉ መድረክ በሚደርስባቸው ጫና የተወሰኑ ኃያላን ሀገራት ወይም ቡድኖች መጠቀሚያ መሆን የለባቸውም ብለዋል፡፡

ቻይና በተመድ ምን ጊዜም ለታዳጊ ሀገራት ድምጽ እንደምትሆንም ነው የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያረጋገጡት፡፡

ቻይና ከታዳጊ ሀገራት ጋር በትብብር እና በአብሮነት ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ዋንግ ዪ በበይነ መረብ በተካሄደው ውይይት የታይዋንን ጉዳይና የቻይናን ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ልዑካኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ይሁንታ ያገኘውን የ”አንድ ቻይና” መርህ መጣስ የሌለበት የቻይና ፖለቲካዊ መሠረት ነው ብለዋል፡፡

ቻይና ከሀገራት ጋር የምታደርገው የሁለትዮሽ ግንኙነትም ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው መጠቆማቸውን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.