Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የመምህራንን ቀን ለማክበር መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዘንድሮ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን እንዲከበር መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ መምህራን ትውልድን በመቅረፅ ውስጥ ትልቅ ሚና ስላላቸው ለመምህራን አስፈላጊውን እውቅና እና ክብር መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መንግስትም ከዘንድሮ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን እንዲከበር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ቀኑን መምህራንን በማክበር፣ በማሰብ እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎችን በማቅረብ እና የፓናል ውይይት በማድረግ ታስቦ እንደሚውል ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ በንቲ በበኩላቸው ቀኑን ከማክበር ባሻገር ቀድሞ የነበረውን የመምህራንን ክብር እና ጥያቄ ለመመለስ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የመምህራን ቀኑ ለአንድ ወር ያህል ወጥነት ባለው መልኩ ከትምህርት ቤት እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.