Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕን ለመክሰስ የአሜሪካ ሴኔት አብላጫ ድምጽ ማግኘት አልቻለም ተባለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ሴኔት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አመጽ አነሳስተዋል በሚል ለመክሰስ ያደረገው ጥረት አብላጫ ድምጽ ሳያገኝ መቅረቱ ተነገረ፡፡

ሆኖም ሴኔቱ ትራምፕን ለመክሰስ ከ100 አባላቱ ውስጥ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ያስፈልገው ነበር ተብሏል፡፡

በአሁኑ የሴኔቱ ምርጫ ሰባት ሪፓብሊካኖችን ጨምሮ በ57 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ 43 በመቶ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ትራምፕን ለመክሰስ 10 ተጨማሪ ድምጾች ማግኘት እንዳልቻለ ነው የተገለጸው፡፡

የሴኔቱን ድምጽ ተከትሎ ትራምፕ የክስ ሂደቱን የሚነቅፍ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት በውጤቱ ዳግም ለምርጫ መወዳደር ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.