Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ በቻይና የባንክ ደብተር አላቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናን በመተቸት የሚታወቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ የባንክ ደብተር እንዳላቸው ኒውዮርክ ታይምስ ዘገበ፡፡

እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ፕሬዚዳንቱ በቻይና የባንክ ደብተር እንዳላቸው አምነዋል፡፡

የባንክ ደብተሩ በትራምፕ ዓለም አቀፍ የሆቴሎች አስተዳደር ስር ነበር ተብሏል፡፡

ከ2013 እስከ 2015 ድረስም የአካባቢው ግብር እንደተከፈለበትም እንደሚያሳይ ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተደጋጋሚ የአሜሪካ ኩባንያዎች በቻይና መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰሳቸው ክፉኛ ሲያብጠለጥሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከእርሳቸው የስልጣን ዘመን በኋላም ሁለቱ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ወደ ንግድ ጦርነት መግባታቸው ሌላኛው ጉዳይ ነው፡፡

የትራምፕ ቃል አቀባይ የባንክ ደብተሩ የተከፈተው በእስያ ሆቴል ለመክፈት የሚያስችል ሁኔታ ስለመኖሩ ለማወቅ በማሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ የተሰማው በትራምፕና በተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን መካከል የሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 12 ቀናት ብቻ ሲቀሩት ነው፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.