Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ዕቅድን ማክሰኞ ይፋ እንደሚያደርጉ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ዕቅድን ማክሰኞ ይፋ እንደያሚደርጉ ገለፁ።

ፕሬዚዳንቱ የሰላም እቅዱን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የምርጫ ተቀናቃኛቸው ቤኒ ጋንትዝን በነጩ ቤተ መንግስት ከማነጋገራቸው ቀደም ብለው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ትራምፕ በንግግራቸው ፍልስጤማውያን በሚያቀርቡት የሰላም እቅድ ላይ አሉታዊ አስተያየት ሊሰጡ እንደሚችሉ አንስተዋል።

ፍልስጤማውያኑ የሰላም ዕቅዱ ከመውጣቱ አስቀድሞ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፥ ትራምፕም ከፍልስጤማውያን ጋር ጊዜውን ጠብቀው እንደሚነጋገሩም ነው የገለጹት።

አዲሱ የሰላም እቅድ ትልቅ እና ለፍልስጤማውያኑ ጠቃሚ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

የፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ቃል አቀባይ ናይል አቡ ሩዴይነህ በበኩላቸው እስራኤልና አሜሪካን አስጠንቅቅዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.