Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር በሚለጠፉ መረጃወች ላይ የሚሰጡ ምላሾችን መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ሊሞክር ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ትዊተር ተጠቃሚወች የሚለጥፏቸውን መረጃወች ተከትሎ የሚሰጡ ምላሾችን መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ሊሞክር መሆኑን አስታወቀ።

ኩባንያው ሙከራው ደንበኞች በነጻነት እንዲሳተፉ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም ገልጿል።

ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች የሚለጥፏቸውን መረጃዎች መሰረት አድርገው የሚሰጡ ምላሾችን መቆጣጠርና መገደብ የሚያስችለውን ሙከራ አደርጋለሁ ብሏል።

የአሁኑ እርምጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበራዊ ትስስር ገጾች በበይነ መረብ አማካኝነት የሚፈጸምን ዘለፋና ማንቋሸሽ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል እየቀረበ ያለውን ወቀሳ ተከትሎ የሚወሰድ ነው ተብሏል።

በቅርቡ ይሞከራል በተባለው አዲስ አሰራር ተጠቃሚዎች በአራት አማራጮች ለተለጠፉ መረጃዎች መልስ እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም ነው ኩባንያው የገለጸው።

በዚህም ዓለም አቀፍ በሆኑ ገጾች ላይ ማንኛውም ሰው ምላሽ መስጠት የሚችል ሲሆን፥ ቡድን አልያም የማህበረሰብ ገጾች ላይ ለተለጠፉ መረጃዎች ደግሞ የዛ ቡድን ተከታይና በመረጃው ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎች ብቻ ምላሽ እንዲሰጡ ያስገድዳል።

በተጨማሪም መወያያ አጀንዳዎችና ጉዳዮች ላይ ደግሞ በዛ መወያያ ሃሳብ ላይ የተጠቀሱ አካላት ብቻ ምላሽ ይሰጣሉ።

የተለጠፉ መግለጫዎች ላይ ደግሞ ማንኛውም አካል ምላሽ እንዳይሰጥ ይደረጋል ብሏል ትዊተር ባወጣው መግለጫ።

ኩባንያው ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች ገጻቸው ላይ ለለጠፉት መረጃ የሚሰጡ ምላሾችን መደበቅ እንዲችሉ የሚያግዝ አሰራር ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.