Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አዶናይ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ አዶናይ ወንድወሰን ለማንቼስተር ዩናይትድ ፈረመ፡፡

በዜግነት እንግሊዛዊ የሆነው የ16 ዓመቱ አዶናይ ከክለቡ ጋር ለሦስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡

በግራ መስመር ቦታ ላይ የሚጫወተው አዶናይ በተለያዩ ክለቦች ውስጥ ትኩረት አግኝቶ እንደነበርም ነው የተገለጸው፡፡

ላለፉት ሁለት የውድድር ዓመታትም በቼልሲ አካዳሚ አሳልፏል፡፡

በአካዳሚ ቆይታውም ያሳየውን ብቃት ተከትሎ በ2019/2020 የውድድር ዘመን የዓመቱ ወጣት ታዳጊ ተብሎ ተመርጧል፡፡

በተጨማሪም በውድድር ዓመቱ ከ50 ሜትር ርቀት ላይ ያስቆጠረው ጎል የዓመቱ ድንቅ ጎል በሚል ተመርጣለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.