Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለቱኒዚያ 100 ሺህ የኮሮና ክትባት ልትለግስ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ለሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ቱኒዚያ 100 ሺህ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመለገስ መወሰኗ ተገለፀ፡፡
እርዳታው በቱኒዚያ እና በቻይና መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት በመመልከት እና ቱኒዚያ ወረርሸኙን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ታስቦ የተሰጠ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ቻይና ቱኒዚያ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች ተብሏል፡፡
የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ የሁለቱን ሃገራት ቀጣይ ትብብር ለሚያንፀባርቀው ለዚህ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.