Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ፈረመች።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛዎ ዚዩሃን እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የድጋፍ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
ድጋፉ፥ ቻይና የአፍሪካ አገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ቃል መግባቷን ተከትሎ የተደረገ እንደሆነ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተመልክቷል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የቻይና መንግሥት ከዚህ ቀደምም ለአራት ተከታታይ ጊዚያት የሲኖፋርም ክትባት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
የአሁኑ የ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ድጋፍ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባትን ተደራሽነት ለማስፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል።
የቻይና መንግስት እስካሁን 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማደረጉን ያስታወሱት ሚኒስትሯ፥ ለዚህ ያልተቋረጠ እገዛም የኢትዮጵያ መንግስት ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።
ኢትዮጵያና ቻይና ከጤናው ዘርፍ ባለፈ በሌሎችም መስኮች ያላቸው ትብብርና አጋርነት ይበልጥ እየተጠናከረ ይገኛል ሲሉም አክለዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛዎ ዚዩሃን በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደግፋለን ማለታቸውንም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከ50 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.