Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለ6 ወር የጠፈር ምርምር ሰራተኞችን ወደ ህዋ ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና ለ 6 ወር የጠፈር ምርምር ተልዕኮ ሰራተኞቿን ወደ ህዋ መላኳን አስታወቀች፡፡
ሀገሪቱ የምሕዋር ግንባታዋን ወደ ማጠናቀቁ በተቃረበችበት እና በጠፈር ምርምር ውስጥ አዲስ ሪከርድ ለማስመዝገብ ማቀዷን ተከትሎ ነዉ ሶስት የጠፈር ተመራማሪዎቿን ወደ ህዋ የላከችዉ።
ሶስቱን ሳይንቲስቶች የያዘዉ የሄንዙ – 13 መንኮራኩር ምሽት 12፡25 ቦታዉ ይደርሳል ነዉ የተባለዉ፡፡
ሳይንቲስቶቹ በህዋ ቆይታቸዉ ሁለት የሳተላይት ሥራዎችን አከናውነው 10 ሜትር (33 ጫማ) ሜካኒካል ክንድ የህዋ መረማመጃ እንደሚገነቡ ተገልጿል።
የቻይና ወታደራዊ ኃይልም የጠፈር መርሃግብር ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አቅም ግንባታ ዉስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብዙ ሠራተኞችን ወደ ጣቢያው ለመላክ አቅዷል።
ሄንዙ-13 መንኮራኩር ደግሞ የህዋ ሳይንስ ተማራማሪዎችን ያጓጓዘ 5ኛዉ መንኮራኩር መሆኑ ታዉቋል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.