Fana: At a Speed of Life!

ቻይና እና ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት በኋላ የመጀመሪያቸውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት በኋላ የመጀመሪያቸውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለፀው፥ የቻይና እና ሩሲያ አየር ኃይሎች በዛሬው ዕለት በጃፓን ባህር ፣ በምስራቅ ቻይና ባህር እንዲሁም በፓስፊክ ውቅያኖስ ባህር ላይ የጋራ የአየር ቅኝት አድርገዋል፡፡

የተደረገው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ከደረገች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ራስን ለመከላከል የተደረገ ወታደራዊ ልምምድ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስተወቀው፡፡

ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በ2019፣ 2020 እና 2021 ራስን የመከላከል በሚል ተመሳሳይ ወታደራዊ ልምምድ በየዓመቱ አጋማሽ ሲያደርጉ እንደነበር ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል፡፡

ሩሲያ የካቲት 24 በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ ከምዕራባውያን ሀገራት ከፍተኛ ማዕቀብ ሲገጥማት፥ በቤጂንግ በበኩሏ ሁለቱም ወገኖች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ስታሳስብ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.