Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከኒውክሌር የኤሌክትሪክ ኃይል ማበልፀጓን እንደምትገፋበት አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኒውክሌር የምታበለፅገውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማሳደግ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡

በዚህ ዓመት 5 ወራት ብቻ ቻይና በሠዓት 166 ነጥብ 3 ቢሊየን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከኒውክሌር ኃይል ማበልጸግ መቻሏን የቻይና የኒውክሌር ኃይል ማኅበር አስታውቋል፡፡

ቻይና 55 ነጥብ 81 ሚሊየን ኪሎ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 54 በሥራ ላይ የሚገኙ የኒውክሌር ኃይል ማዕከላት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ ማዕከላት የሚገኘው የኃይል አቅርቦትም ቻይናን በዘርፉ ከተሰማሩ የዓለም ሀገራት የ3ኛ ደረጃን እንድትይዝ አስችሏታል ተብሏል፡፡

ከኒውክሌር የሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል የማይቆራረጥ ፣ አስተማማኝ እና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው በመሆኑ የቻይናን የአረንጓዴ ልማት ዕቅድ ለማሳካት ተሥፋ ከተጣለባቸው የኃይል ምንጮች አንዱ መሆኑን የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው።

እስካሁን ቻይና ከዓለም ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያለውን የድንጋይ ከሰል ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት በከፍተኛ ደረጃ የምትጠቀም ሀገር ናት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.