Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላት የሻከረ ግንኙነት በአየር ንብረት የሚደረገውን ትብብር አደጋ ላይ እንዳይጥለው አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የአየር ንብረት ትብብር ፈፅሞ ከሰፊው የቻይናና የአሜሪካ ግንኙነት ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል ለአሜሪካ የአየር ንብረት መልዕክተኛ ጆን ኬሪ ተናግረዋል።

አያይዘውም እየላላ የመጣው የአሜሪካ እና የቻይና ግንኙነት የዓለም ሙቀት መጨመርና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ያኮስሳል ነው ያሉት፡፡

የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል አሜሪካ ፈጣን እርምጃ እንድትወስድ ረቡዕ ዕለት ጠይቀዋል፡፡

ጆን ኬሪ በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የሚከሰቱ አደጋዎች በሚገባቸው ልክ እንዳልታዩና በጉዳዩ ላይ መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

መልዕክተኛው ቻይና ለጉዳዩ የሰጠችውን ትኩረት አድንቀው ልቀትን ለመቀነስ እየሰራች ያለውን ስራ አጠናክራ እንድትቀጥልና ተጨማሪ እርምጃዎችን እንድትወስድም ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.