Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከአንድ የአሜሪካ ሥጋ አቅራቢ ኩባንያ ምርት እንዳይገባ አገደች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና ከአንድ የአሜሪካ ኩባንያ የቁም እንስሳት የሥጋ ውጤት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ አግዳለች፡፡

የቻይና የጉምሩክ ባለሥልጣናት ከኩባንያው የሚገቡ የሥጋ ውጤቶችን ያገዱት “ራክቶፓሚን” የተሠኘ የተከለከለ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው መሆኑን ዛሬ አስታውቀዋል።

“ራክቶፓሚን” የተሰኘውን የተከለከለ ንጥረ ነገር በእንስሳት መኖ ውስጥ ጨምሮ እንስሳቱን በመመገብ ሥጋቸውን ለወጪ ንግድ ያቀረበው “ኪንግ የስጋ አገልግሎት” የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

የቻይና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ የግብርና ክፍል ማሳወቁን መግለጹንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

ቻይና ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ እርምጃዎችን በአውስትራሊያ እና ሊትዋንያ ሥጋ አቅራቢ ኩባንያዎች ላይም መውሰዷ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.