Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የአሜሪካ -ታይዋን የንግድ ግንኙነት ውይይትን ተቃወመች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ታይዋን በይፋ የጀመሩትን የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት እንቅስቃሴ ቻይና ተቃውማለች፡፡

አሜሪካ እና ታይዋን የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ማዕቀፍ ላይ መደበኛ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷”የአንድ-ቻይና መርህ“ ለቻይና ታይዋን ቀጠና በማንኛውም የውጭ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ውስጥ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ይህን መርህ የሚፃረረው የአሜሪካ ተግባርም ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ እና የንግድ ህግጋትን የጣሰ እና የዓለም የአቅርቦት ሰንሰለትን የሚረብሽ መሆኑን የሚኒስቴሩ መግለጫ አብራርቷል፡፡

አሜሪካ እና ታይዋን የንግድ ግንኙነታቸውን በይፋ ለመጀመር መስማማታቸውም በቀጠናው የተፈጠረውን ውጥረት ይበልጥ እንዳያባብሰው መሰጋቱን አናዶሉ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.