Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመላ ዜጎቼ አያስፈልግም አለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና በዚህ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንጂ ለመላ ዜጎች ክትባቱ እንደማይስፈልግ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጤና ባለስልጣን ገለፁ።
 
የቫይረሱ ክትባት ጥቅም ላይ በሚውልበት ወቅት በሽታውን በመከላከል ሂደት ላይ ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ለሚገኙ እና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥቅም ላይ እንደምታውል ተጠቁሟል።
 
ይህም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሀገሪቱ የተከናወነው ስራ ለፓሊሲ አውጭዎች መተማመን እንደፈጠረላቸው ያሳየ ነው ተብሏል።
 
የቻይና በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ዳይሬክተር ጋው ፉ ሀገራቸው ቫይረሱ በውሃን ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጊዜያት ተፅዕኖውን መቋቋም መቻሏን ተናግረዋል።
 
ክትባቱን ለማህበረሰቡ ጥቅም ላይ ቢውል ከውጪ እና ከጎንዮሽ ጉዳት ጋር ተያይዞ ያለው ተፅዕኖ መታየቱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
 
በመሆኑም በዚህ ደረጃ በዘመቻ ለህብረተሰቡ ክትባት መስጠት አያስፈልግም ያሉት ዳይሬክተሩ ሌላ ወረርሽኝ ከተከሰተ ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብለዋል።
 
ይህ ውሳኔም ቻይና ከምዕራባውያን የተለየ አቋም እንዲኖራት ያደረገ ሲሆን፥ በዋነኝነት ክትባት ለመስጠት ቀጠሮ ከያዘችው አውስትራሊያ እንድትላይ አድርጓታል።
 
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፀደይ ወቅት ጀምሮ መቀነሱ የሚነገር ቢሆንም፤ በተወሰኑ ጊዜያት ውስጥ ከፍ ያለ ስርጭት ተመዝግቦ ነበር።
 
ሆኖም ሀገሪቱ በፍጥነት በወሰደቻቸው አካባቢዎችን የመዝጋት እና የምርመራ ዘመቻ በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለች ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስፍሯል።
 
ዋና ዳይሬክተሩ ሀገራቸው እነዚህ መረጃዎች ቻይና ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መንገዶች እንዳሏት ያመለከቱ ናቸው ብለዋል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.