Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የኮሮና ቫይረስ የህክምና ቡድን ወደ ሆንግ ኮንግ ላከች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኮሮና ቫይረስ የህክምና ቡድን ወደ ሆንግ ኮንግ ላከች፡፡

የህክምና ቡድኑ 60 ዓባላትን የያዘ ሲሆን 7 የጤና ባለስልጣናትም ተካተውበታል፡፡

ቻይና ወደ ሆንግ ኮንግ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የህክምና ባለሙያ ቡድን ስትልክ ይህ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል፡፡

የህክምና ባለሙያዎች ወደ ሆንግ ኮንግ የተጓዙት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ እንደሆነው ተነግሯል።

ነገር ግን አንዳንድ የአካባቢው የምክር ቤት አባላት በዚህ አጋጣሚ ቻይና ግለሰቦችን ለመከታተል የዲ ኤን ኤ ናሙናዎችን ልትሰበስብ ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላቸው ተነግሯል፡፡

የሆንግ ኮንግ መንግስት ግን ይህን ውድቅ አድርጎታል፡፡

በሃገሪቱ አሁን ላይ 3 ሺህ 512 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 37 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.