Fana: At a Speed of Life!

ኅብረተሰቡ ለገቢ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኑን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች መካከል በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኖቹን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታው በመጪው እሁድ ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።

ጨዋታው በዋናነት የተዘጋጀው በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ሲሆን፥ ጎን ለጎን በዳያስፖራውና በአገር ውስጥ በሚኖረው ማኅበረሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳ አስተባባሪው ማስተር ሄኖክ መገርሳ ተናግረዋል።

እሑድ ከቀኑ 7፡00 ሠዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲዮም በታዳጊዎች እንዲሁም በኮሜዲያንና በደጋፊዎች መካከል የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።

ጨዋታውን ለመታደም የመግቢያ ዋጋው የአገር ውስጥ ደጋፊዎች ለክቡር ትሪቡን 1 ሺህ ብር፣ ለጥላ ፎቅ 500 ብር ለቀሩት ቦታዎች 100 ብር መሆኑም ተገልጿል ።

ዳያስፖራ ተመልካቾች ክቡር ትሪቡን 100 ዶላር፣ ጥላ ፎቅ 75 ዶላርና ሌሎች ቦታዎች 50 ዶላር መግቢያ የሚከፍሉ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የመግቢያ ትኬቱ በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎችና በአይዞን ኢትዮጵያ የገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ ኦን ላይን እንደሚሸጥም አቶ ቴድሮስ ባጫ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.