Fana: At a Speed of Life!

ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የሚዘጉ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የሚዘጉ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ፡፡

ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ በሚደረገው ውድድር የሃገሪቱን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዳያስፖራዎች፣ የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም በርከታ ተሳታፊዎች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውድድሩ የሚጠበቅበትን ዓላማ እንዲያሳካና በሰላም እንዲጠናቀቅ በፌዴራልና በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የፀጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚጀመረው ወድድር በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ ፣ በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ፣ጎማ ቁጠባ በፍል ውሃ በማድረግ በካዛንቺስ ፣ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ባንቢስ በመታጠፍ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዲችሉ ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፦

ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር፤ ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ፤ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባበይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ገብርኤል መሳለሚያ፤ ከሳር ቤቶች አደባባይ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ፤ ከካርል አደባባይ ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚወስደው መንገድ ልደታ ፀበል፤ ከጦር-ኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ፡-

እንዲሁም ከሜክሲኮ ልደታ ኮንደሚኒዬም መብራት፤ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤ ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)፤ ከቸርቸር ጎዳና ወደ አምባሳደር ፣ ከሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ አገር አስተዳደር/ኢምግሬሽን/ መብራት ፤ ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ፤ መድሃኔዓለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ፡-
ከጠዋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም አሽከርካሪዎች የውድሩሩ ተሳታፊዎች ወደ ሚያልፉባቸው መንገዶች ተሽከርካሪ ይዞ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.