Fana: At a Speed of Life!

ናይጀሪያ በድፍድፍ ነዳጅ ስርቆት ምክንያት 1 ቢሊየን ዶላር ማጣቷን አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጀሪያ በፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያው ሩብ አመት በድፍድፍ ነዳጅ ስርቆት ምክንያት 1 ቢሊየን ዶላር ማጣቷን የሀገሪቱ የነዳጅ ተቆጣጣሪ ድርጅት አስታወቀ።

ናይጀሪያ በሩብ አመቱ 141 ሚሊየን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማምረቷን ድርጅቱ ገልጿል።

ይሁን እንጅ ከዚህ ውስጥ 9 ሚሊየን በርሜል ድፍድፍ ነዳጁ መሰረቁንም ነው የገለጸው።

ይህም በገንዘብ ሲተመን 1 ቢሊየን ዶላር መሆኑን ጠቅሶ፥ ስርቆቱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ ሊጎዳው እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በተያዘው የፈረንጆቹ የመጀመሪያ ሩብ አመት በናይጀሪያ 108 ሺህ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በርሜል የተሰረቀ ሲሆን፥ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ5 ሺህ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።

ናይጀሪያ በየአመቱ በስርቆት ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠር በርሜል ድፍድፍ ነደጅ እንደምታጣ የሬውተርስ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.