Fana: At a Speed of Life!

ናይጀሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባት ሶስተኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ናይጀሪያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው የተገኘባት ሶስተኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች።

የቫይረሱ ተጠቂ የሆነው ግለሰብ ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን፥ ናይጄሪያ ውስጥ የሚሰራና ከሶስት ቀን በፊት ከሚላን ወደ ሌጎስ የመጣ ነው ተብሏል።

የናይጄሪያ ጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናትም ግለሰቡ ሌጎስ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ገልጸዋል።

ከታማሚው ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ሰዎችን መለየት መጀመራቸውንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

መንግስትም የአስቸኳይ ጊዜ ዘመቻ እቅድ አውጥቶ ወደ ስራ ገብቷልም ነው ያሉት።

ከዚህ ቀደም ግብፅ እና አልጄሪያ የቫይረሱ ተጠቂ የተገኘባቸው ሃገራት ነበሩ።

ከናይጀሪያ በተጨማሪም ኒውዝላንድ እና ሉቴኒያ የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

አሁን ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከቻይና ውጭ ደግሞ 60 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

በቫይረሱ ሳቢያም የዓለም አቀፉ የአክሲዮን ገበያ መቀዛቀዝ ማሳየቱም እየተነገረ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.