Fana: At a Speed of Life!

ናይጄሪያ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውጭ ምግብ የምታስመጣበት ገንዘብ የላትም-ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት  ሙሀመዱ ቡሀሪ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ችግር አገሪቱ  ከውጭ ምግብ የምታመጣበት ምንም ገንዘብ እንደሌላት ገለጹ ፡፡

ስለሆነም አርሶ አደሮች አገሪቱን ለመመገብ የሚያስችል በቂ ምርት ማምረት አለባቸው ብለዋል ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ።

በአፍሪካ በህዝብ ብዛት በአንደንነት የምትቀመጠው ናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሀገሪቱ  የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩም ባለፈ የምግብ ዋስትና  ችግር ስጋቶች እየጨመሩ  መምጣታቸው ተነግሯል።

እንደተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ  ፕሮግራም  አስተያየት÷ የናይጄሪያ አርሶ አደሮች   ከኮቪድ-19  ወረርሽኝ ቀውስ በፊትም ቢሆን የሀገሪቱን  200 ሚሊዮን ያህል ህዝብ ፍላጎት ለማርካት አለመቻላቸውን ገልጿል፡፡

ምንም እንኳን በሀገሪቱ የግብርናው ዘርፍ በርካታ ሰዎችን የሚያሳትፍ ዋነኛው የስራ መስክ ቢሆንም  የአገሪቱ ኢኮኖሚ በነዳጅ ገቢ ላይ ትኩረት በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ለዓመታት ችላ ብሎት መቆየቱም ነው የሚገለጸው።

ናይጄሪያ ባለፈው  የፈረንጆች ዓመት  ከሌሎች ሀገሮች ጋርቨ የሚያዋስናትን የሀገሪቱን የመሬት ድንበሮች በመዝጋት ከታይላንድ  በሕገወጥ መንገድ የሚገቡ የሩዝ ምርቶችን  በማስቀረት የአገር ውስጥ ሩዝ ምርትን ለማሳደግ ጥረት ስታደርግ መቆየቷም ነው የተገለጸው።

በመሆኑም በወደቦች  በኩል ብቻ የውጭ ሩዝ  ምርት ወደ ሀገሪቱ የሚገባ ከመሆኑም ባለፈ ከፍተኛ ግብር በምርቱ ላይ በመጣሉ ለዋጋ መጨመሩ ምክንያት ነው የተባለው ፡፡

ሀገሪቱ  ከውጭ በሚገባ የሩዝ ምርት ላይ እገዳ ከመጣሏ በፊት በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ ሩዝ ከታይላንድ  ወደ ሀገር ውስጥ ታስገባ ነበርም ነው የተባለው፡፡

የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በናይጄሪያ የምግብ ዋጋ ከፍ ከማለቱም ባሻገር   በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ዝቅ በማለቱ የተነሳ የአገሪቱ መንግስት የሚያገኘው ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱም ይነገራል።

የዓለም አቀፉ  የገንዘብ ድርጅት(አይ.ኤም.ኤፍ) የአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ናይጄሪያ በዚህ ዓመት (በፈረንጆቹ 2020  ) ኢኮኖሚዋ በ 1ነጥብ 5 በመቶ እንደሚያሽቆለቁልም ነው የተነበየው።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.