Fana: At a Speed of Life!

ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወደ ተከሰተባቸው ሀገራት የሚጓዙ መንገደኞች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወደ ተከሰተባቸው ሀገራት የሚጓዙ መንገደኞች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲቲዩት ይፋ አድርጓል፡፡

ጥንቃቄዎቹም፡-

• የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚታይባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

• እጅን በሳሙና እና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

• ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

• በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

• ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ሕክምና ተቋማት፣ ከጉዞ ማሕበራት፣ ከአየር መንገድ፣ ከመዳረሻ ቦታዎች ወይም ከሌሎች የጤና መረጃ ምንጮች ስለ በሽታው በቂ መረጃ ማግኘት እና ራሳቸውን ከበሽታው መከላከል ይጠበቅባቸዋል፡፡

በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ደግሞ ፡-

• ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም፣ ትኩሳትና እንደ ሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣

• የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት (14) ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ ሃገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤

• በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት መሽፈን፣

• አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልክቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ ሃገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት ጀምሮ ለህክምና ወደ ግልም ሆን የመንግስት ተቋማት የመጣ ታማሚ ሲኖር ወዲያውኑ በቅርበት ላሉ የጤና ፅህፈት ቤት (መምሪያ፣ ቢሮ ) ማሳወቅ ይኖርበታልም ነው የተባለው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0112765340 ወይም በኢሜል አድራሻ phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ወይም መላክ ይቻላል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.