Fana: At a Speed of Life!

ኖኪያ 3310 ወደ ገበያ  ከገባ 20 ዓመታትን አስቆጠረ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ከሚያስታውሷቸው የመጀመሪያዎቹ ስልኮች መካከል አንዱ የሆነው ኖኪያ 3310 ወደ ከገበያ  20 ዓመታትን አስቆጠረ፡፡

በፊኒላንድ ኩባንያ የተመረተው ኖኪያ 3310 በአውሮፓውያኑ 2000  ነበር ይፋ የሆነው፡፡

የሞባይል ስልኩ ሲም ካርዱ ውስጥ 250 የስልክ ቁጥሮችን የመመዝገብ አቅም ነበረው፡፡

እንዲሁም ተጠቃሚዎች የራሳቸውን የስልክ ጥሪ ወይንም ሪንግ ቶን በስልካቸው ላይ እንዲሞላ በማድረጉም ይታወቃል፡፡

ኩባንያው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓለም ዙሪያ 126 ሚሊየን ኖኪያ 3310 ስልኮችን መሸጡን ይፋ አድርጓል፡፡

ይህም በዓለም ላይ በብዛት ከተሸጡ ስልኮች መካከል አንዱ ያደርገዋል፡፡

ኖኪያ 3310 መተግበሪያ፣ አራተኛና አምስተኛ ትውልድ ከመምጣታቸው በፊት የነበረ ሲሆን ውስን ነገሮችን ነበር የያዘው፡፡

ስልክ መደዋወል፣ የጽሑፍ መልዕክት መለዋወጥ እንዲሁም የእባብ (ስኔክ) ጨዋታዎችን መያዙ ብዙዎች ያስታውሳሉ፡፡

ከ2017 ወዲህ ደግሞ ዳግም ወደ ገበያ መመለሱ ያስታወቀ ሲሆን÷ ሁለት ሲም ካርድ የሚይዝ፣ 2 ፒክስል ካሜራ ያለው እና ሚሞሪ እንዲቀበል ተሻሽሎ መጥቷል፡፡

 

ምንጭ፦ሜትሮ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.