Fana: At a Speed of Life!

አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው – ወይዘሮ ሙፈሪሃት

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ጉዳዮች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በሰለጠነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

የሠላም ሚኒስትሯ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተቋማቸው ባለፉት ሶስት ዓመታት በሃገሪቷ ዘላቂ ሠላም ማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

“ለዘመናት የተከማቸ ችግርን በአንድ ጀምበር መፍታት አይቻልም” ያሉት ሚኒስትሯ፥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በሰለጠነ መንገድ በውይይት የመፍታት ልምድ ማዳበር አንደኛው መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ በሚኒስቴሩ የሚዘጋጁ ስልጡን የውይይት መድረኮች ውጤት እያስገኙ መሆኑን ነው የገለጹት።

በእነዚህ የምክክር መድረኮች ምሁራንን ጨምሮ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞችና በሁሉም የሃገሪቷ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ናቸው።

ሚኒስትሯ በውጤታማነቱ ስምንት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት የሚሳተፉበትና የሚያስተባብሩትን የውይይት መድረክ ለአብነት ጠቅሰዋል።

በሌላ መልኩ ከሃገራዊ ለውጡ በኋላ በውጭ የሚኖሩ የታጠቁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲወዳደሩ የማሳመኑ ስራ ሌላው ውጤት መሆኑን አንስተዋል።

መሰል ውይይቶች አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ ከመፍታት ባለፈ ለዘላቂ ሠላም ግንባታና ለዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸውም ነው የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.