Fana: At a Speed of Life!

አለኝታ የበጎ አድራጎት ድርጅት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አለኝታ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደባርቅ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የሥራ ኀላፊዎች በደባርቅ ከተማ በመገኘትም ድጋፉን ለተጎጅ ወገኖች አድርሰዋል፡፡
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብረሃም እንዳለው÷ አለኝታ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሀገር በቀል የሆነና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን ነድፎ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው በሀገሪቱ ላይ ችግሮች ሲከሰቱ ድጋፎችን በማሰባሰብ ለተቸገሩት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 90 ኩንታል የፊኖ ዱቄት፣10 ኩንታል የህፃናት አልሚ ምግብ፣ ከሕብረተሰቡ የተሰበሰበ አልባሳትና የሴቶች ንፅሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
ሥራ አሥኪያጁ ድጋፎች ከማኅበረሰቡ የተውጣጡና በወረራው ተጎጅ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሕይወት ለማዳን የሚደረጉ በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ድጋፎች በተገቢው መንገድ ተጎጅ ለሆኑና ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲደርሱ በማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ በለጠ ጥላዬ ከተለያዩ አካላት ለተጎጅ ወገኖች የሚመጡ ድጋፎች በአግባቡ እንዲደርሱ የመንግሥትን አሠራር መከተሉ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ከ130 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች በሚገኙበት ደባርቅ ከተማ የሚመጡ ድጋፎች በመንግሥት ተቋም አደረጃጀት አማካኝነት ድጋፍ የደረሳቸውና ያልደረሳቸው፤ ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው እየተለዩ ሊደገፉ ይገባል ብለዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
በስርጭቱ ሂደት አዋጪው መንገድ በመንግሥት ተቋም አደረጃጀት ተመርቶ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን እየፈቱ ድጋፎችን ለተጎጅው ማድረስ ስለሆነ በዚህ መንገድ ሥራዎች በአግባቡ እየተከናወኑ ነውም ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.