Fana: At a Speed of Life!

አልጄሪያ በአረብ ሊግ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን የተሳሳተ አቋም እንደምታስተካክል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲና ላይቤሪያ ጋር ውይይት ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለአቀባይ አምሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምሳደሩ በመግለጫቸው በቀጣይ አልጄሪያ በሊቀመንበርነት በምትመራው አረብ ሊግ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን የተሳሳተ አቋም እንደምታስተካክል ተስማምተዋል።

ከቡሩንዲ ጋር በተደረገ ውይይትም የታላቁ የህዳሴ ግድብ በአፍሪካዊያን መፍትሄ እንዲያገኝ እንደምትደግፍ ሃገሪቱ መግለጿን የተናገሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የላይቤሪያ መንግስትም ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም አረጋግጧል ብለዋል።

እንዲሁም ከቡሩንዲ ጋር በተደረገ ውይይት ቀጠናዊ ግንኙነትን ለማሳደግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ውይይት የተደረገባቸው ሀገራትም የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን መፈታት አለባቸው የሚል ፅኑ አቋማቸውን አንፀባርቀዋል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፡፡

የህብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ጠዋት ባደረጉት ምክክር የምርጫ ርዕሰ ጉዳይ ያነሱ ሲሆን የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችም ሰይመዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.