Fana: At a Speed of Life!

አመታዊው የዘመናዊ ስልኮች ማሳያ ዝግጅት በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በየአመቱ በስፔን ባርሴሎና የሚካሄደውና የዓለማችን ትልቁ የዘመናዊ ስልኮች ማሳያ የሆነው የሞባይል ወርልድ ኮንግረስ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት መሰረዙን አዘጋጆቹ ገለጹ።

በዚህ ዓመታዊ ፕሮግራም ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 6 ሺህ የሚሆኑት ከቻይና የሚመጡ ናቸው ተብሏል።

በርካታ ኩባንያዎችም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ሲሆን፥ የስፔኗ ባርሴሎና በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆኗ ይነገራል።

ፌስቡክ፣ ኤል ጂ፣ ኖኪያ እና ሶኒን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ኩባንያወች ከዝግጅቱ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።

ኩባንያዎቹ በዚህ ወቅት ሰራተኞቻቸውን ወደ ስፍራው መላክ ሃላፊነት የጎደለውና ተገቢነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የስፔን የጤና ሚኒስትር ሳልቫዶር ኢላ በበኩላቸው ተሳታፊዎቹ እንዲረጋጉና በስፔን የጤና ስርዓት እምነት እንዲያሳድሩ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.