Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ሀሰተኛ መረጃዎችን ያሰራጫሉ ያለቻቸውን የኢራን ድረ ገጾች አገደች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣2013 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ ሀሰተኛ እና የተዛቡ መረጃዎችን ያሰራጫሉ ያለቻቸውን የኢራን ድረ ገጾች ከኢንተርኔት ማገዷ ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ ባለቤትነታቸው የኢራን መንግስት የሆኑ 33 ድረ ገጾች እና የሃውቲ አማጺያን አቀንቃኝ የሆኑ 3 ገጾች ከበይነ መረብ መውረዳቸውን አስታቀውቋል፡፡

ከታገዱት ድረ ገጾች መካከልም በኢንግሊዘኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያሰራጨው እና ባለቤትነቱ የኢራን መንግስት የሆነው ፕረስ ቲቪ አንዱ ነው፡፡

ባለቤትነቱ በኢራን የሚደገፈው የሃውቲ አማጺያን ቡድን አቀንቃኝ የሆነው አል ማሲራህ ቲቪም በአሜሪካ መንግስት ከኢንተርኔት እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

አሁን ላይም አብዛኞቹ ድረ ገጾች በሌላ ገጽ ወደ ኢንተርኔት ተመልሰው መረጃ ማሰራጨት መጀመራቸውን ለተከታዮቻቸው ማስተዋወቅ ጀምረዋል፡፡

ገጾቹ አሜሪካ እና ኢራን በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ዙሪያ የሚደረገውን ድርድር እንደ አዲስ ለመጀመር ውጥረት ላይ ባሉበት ወቅት መታገዳቸውም ችግሩን ይበልጥ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡

ምንጭ÷ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.