Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ሁዋዌ ላይ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለሁዋዌ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ መሆኑን አስታወቀች።

አሜሪካ የምታመርታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የተመረቱ የቴሌኮም ምርቶችን ለግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያ እንዳይሸጡ ለማገድ ስለመዘጋጀቷም ነው የገለጸችው።

የትራምፕ አስተዳደር ሁዋዌ የሃገሪቱን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል በሚል ኩባንያው ላይ ጫና እያሳደረ ነው።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ኩባንያውን በጥቁር መዝገብ አስፍሮት እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይም ለኩባንያው ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ሃገራት የሚጓጓዙ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶች ላይ ገደብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት አሁን ባለው ህግ የአሜሪካ የቴክኖሎጅ ምርቶች ከፍ ያለውን ዋጋ ከያዙ ወደ ቻይና የሚላኩ የሌሎች ሃገራትን የቴክኖሎጅ ምርቶች የማገድ ወይም የማስገቢያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል።

አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው።

አሜሪካ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ በተለይም ምዕራባውያን አጋሮቿ እንዳይጠቀሙ እየወተወተች ትገኛለች።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.