Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለዩክሬን 1 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን አንድ ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማድረግ ወሰነች፡፡የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ድጋፉ የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ሚሳኤል፣ የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ጥይቶች እና ሌሎች ጦር መሳሪያዎችን ያካተተ ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ዘመኑን የዋጁ ከመሬት ወደ አየር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎች እና ከ50 በላይ ኤም 113 የተሰኙ ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በድጋፍ ማዕቀፉ ውስጥ መካተታቸው ተጠቁሟል፡፡

ድጋፉ አሜሪካ፥ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ለኪየቭ ያበረከተችውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ መጠን 8 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ያደርሰዋል መባሉን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ፥ዋሽንግተን ለዩክሬን የተራቀቁ ሚሳኤሎችን እና በርካታ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መወሰኗ ግጭቱ ይበልጥ እንዲባባስ መፈለጓን ያሳያል ስትል ታወግዛለች።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.