Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በታይዋን አቅራቢያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደምታደርግ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች እና አውሮፕላኖች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የታይዋን ባህርን እንደሚያልፉ ዋይትሀውስ አስታውቃል።

በአካባቢው የቻይና ወታደራዊ ልምምዶችን ያወገዙት የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ እንደገለጹት፥  የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን)  ‘ዩኤስኤስ ሮናልድ ሬገን’ የተሰኘችውን አውሮፕላን ጫኝ መርከብ እና አጃቢዎቿን ሁኔታውን ለመከታተል በታይዋን አቅራቢያ እንዲሰፍሩ አዟል፡፡

የቻይናን ተቃውሞ ወደ ጎን ያሉት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ሲጎበኙ “ሬገን” እና አጃቢዎቿ በምሥራቅ ቻይና ባህር ተሰማርተው አንደነበረና አሁን ላይም በጃፓን እንደሚገኙ የናግረዋል።

በሁኔታው ክፉኛ የተቆጣችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ሰፊ ልምምዶችን በማድረግ እና በደሴቲቱ አካባቢ በርከት ያሉ ሚሳኤሎችን በመተኮስ ለፔሎሲ ጉብኝት ምላሽ ሰጥታለች ብለዋል።

ውጥረቱ መበርታቱን ተከትሎ፥ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን  የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች ቀደም ብሎ ከታቀደው ረዘም ላለ ጊዜ በአካባቢው እንዲቆዩ  ማዘዝ ብልህነት ነው ሲሉ መወሰናቸውን ቃል አቀባይ ከርቢ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፥ “የቻይና የሚሳኤል ሙከራዎች ኃላፊነት የጎደላቸው እና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከያዝነው የረም ጊዜ ግባችን ጋር የሚጋጭ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ለአሥርት ዓመታት ያህል ታይዋንን በመደገፍ እና ነፃ እና ክፍት የሆነ ኢንዶ-ፓሲፊክን በመከላከል፤ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር በተጣጣመ መልኩ በምዕራባዊ ፓስፊክ ባህር እና ሰማይ ላይ ከመስራት ልንታገድ አይገባም በማለትም ተናግረዋል፡፡

ከርቢ አያይዘውም፡- የአሜሪካ አየር ኃይል የሚኔትማን-3 አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራን ለሌላ ጊዜ ማራዘሙን ያስታወሱ ሲሆን፥  ነገር ግን ይህ ሙከራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚደረግ እና የአሜሪካው የኒውክሌር መከላከያም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ውጤታማ ነው ማለታቸውን የአርቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይና ታይዋንን በመክበብ እያደረገች ያለውን ወታደራዊ ልምምድ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማውገዛቸውንም አልአረቢያ ኒውስ ዘግቧል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የቻይና ወታደራዊ ኃይል የታይዋንን ማዕከላዊ መስመር በተደጋጋሚ ማቋረጡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ዘገባው እንዳተተውም፥ ዛሬ ማለዳ ላይ ወደ 10 የሚጠጉ የቻይና የባህር ኃይል መርከቦች እና 20 ወታደራዊ አውሮፕላኖች የታይዋንን ማዕከላዊ መስመር ማቋረጣቸውን የታይዋን ምንጮች  መናገራቸውም ተዘግቧል።

የሕዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት በ“አንድ ቻይና “ ፖሊሲ እና ‘አንድ አገር፥ ሁለት ፖሊሲ” በሚል መርህ በመመራት ታይዋን የቻይና ግዛት አንድ አካል እንደሆነች በጽኑ እንደምታምን በተደጋጋሚ ገልጻለች።

በርካታ አገሮችም ይህን የአንድ ቻይና ፖሊሲ እንደሚደግፉት ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አሜሪካም  “የሻንጋይ የጋራ መግለጫ” ተብሎ በሚታወቀውና በፈረንጆቹ 1972 ከቻይና ጋር በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንድ ቻይና ፖሊሲን እንደተቀበለችና ታይዋንም የቻይና አካል እንደሆነች እውቅና ሰጥታ እንደነበር ይታወሳል።ለዚህም የዓለም ባንክ ከዚህ በፊት ከመደበው 276 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ 200 ሚሊየን ዶላር መመደቡን አስታውቀዋል።

ተጨማሪ በጀቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወርሽኝ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች  ላይ የፈጠረውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የተፈቀደ መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.