Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በትግራይ ክልል ለመጠለያ አገልግሎት የሚውል 1 ሺህ 500 የፕላስቲክ ጥቅሎችን ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግስት በትግራይ ክልል ለመጠለያ አገልግሎት የሚውል 1 ሺህ 500 የፕላስቲክ ጥቅሎችን ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ይህ የፕላስቲክ ጥቅል በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኩል በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች እንደሚሰራጭ የሚጠበቅ ሲሆን በኢትዮጵያ አሜሪካ አምባሳደር ጌታ ፓሲ ለድርጅቱ አስረክበዋል።

ከፍ ያለ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተነገረለት ይህ ለመጠለያ የሚያገለግል ፕላስቲክ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል እንደሚጓጓዝም ነው የተነገረው።

ከብሄራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የመጠለያ ቁሳቁሶቹ እና አቅርቦቱ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንደሚሰራጩ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ፓሲ በትግራይ ክልል ህግን በማስከበር እርምጃው ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህ የድንገተኛ የፕላስቲክ መጠለያ ለ82 ሺህ 500 ዜጎች የሚሰራጭ ነው ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.