Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በኢራን ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲራዘም ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አሜሪካ በኢራን ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲራዘም ያቀረበችውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረገ፡፡

ምክር ቤቱ ሌሊቱን ባደረገው ስብሰባ ዋሽንግተን በቴህራን ላይ ላለፉት 13 አመታት የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ ይራዘም በሚል ያቀረበችውን ሃሳብ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ብቸኛዋ የአሜሪካን የውሳኔ ሃሳብ የደገፈች ሃገር ሆናለች፡፡

በአንጻሩ ሩሲያ እና ቻይና የውሳኔ ሃሳቡን በመኮነን ተቃውመውታል፡፡

ብሪታንያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይን ጨምሮ 11 ሃገራት ደግሞ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ ተግባራዊ ይደረግ ዘንድ ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት የዘጠኙ ይሁንታ ያስፈልገው ነበር፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.