Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በካሜሩን ከተከሰተው አመፅ ጋር ተያይዞ የቪዛ እገዳ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በካሜሩን ከተከሰተው አመፅ ጋር በተያያዘ በግለሰቦች ላይ የቪዛ እገዳ አድርጋለች፡፡
ሃገሪቱ እገዳውን ያደረገችው በሰሜን ምዕራብ ካሜሩን ሁከት በማነሳሳት በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ በካሜሩን አንግሎፎን ግዛት ውስጥ የቀጠለው ሁከት እንዳሳሰባት ተናግረዋል፡፡
“ሁከት በመቀስቀስ ወይም በማነሳሳት ፣ በሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች የሚፈፅሙ፣ በማስፈራራት ሰላምን የሚያደፈርሱትን እናወግዛለን” ብለዋል ፡፡
የካሜሩን መንግስት እና ተገንጣይ ታጣቂ ቡድኖችም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አመፁን በማስቆም ወደ ድርድር እንዲገቡ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አሜሪካ በካሜሩን ከተከሰተው አመፅ ጋር በተያያዘ የጣለችው የቪዛ እገዳ በስንት ሰዎች ላይ እንደሆነ የተባለ ነገር የለም፡፡
እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች በሚበዙበት የካሜሩን ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሃገሪሩ ክፍል ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ3 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 700 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.